እንኳን በሰላም መጡ ዲላ ከተማ አስተዳደር
ዲላ ከተማ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የግብርና ክላስተር መቀመጫ የሆነች እንግዳ ተቀባይ እና ውብ ናት።
አረንጓዴዋ ከተማ
እንኳን ወደ ዲላ ከተማ በደህና መጡ
ራዕይ እና ተልዕኮ
ራዕይ
ዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ የብልጽግና እና የዘላቂ ዕድገት ምልክት፤ እንዲሁም የዕድል፣ የአካታችነት እና የላቀ የከተማ ኑሮ ጥራት የሚንፀባረቅባት ከተማ ሆና ማየት።
ተልዕኮ
የዲላን ገጽታ ለመገንባት፣ ኢንቨስትመንትን እና ትብብርን ለማሳደግ የአካባቢ፣ የአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ አጋርነቶችን ማጠናከር።
በሁሉም የህዝብ አገልግሎቶች ፍትሃዊነትን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈን።
ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ፣ የከተማ ልማት አገልግሎቶችን ለዜጎች መስጠት።
የመሪዎች መልዕክቶች
ዶ/ር መስፍን ደምሴ
የዲላ ከተማ ከንቲባ
ዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ረጂዮ ፖሊሲ ከተሞች መካከል እንዷ ሰትሆን አሁን ላይ የክልሉ ግብርና ክላስተር ማዕከል የበርካታ ብሄር፤ብሄረሰቦች በአብሮነት የምኖሩባት ከተማ ነች። ከተማችን የመደመር መንግሥት ለከተሞች ዕድገት የሰጠው ትኩረት መነሻ የከተማችን ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ እና ለነዋሪዎች ምቹ የቱሪስቶች መዳረሻ እንዲሆኑ እና ፀጋቸውን ለይተው እንዲያድጉ የተወሰደው እርምጃም ውጤት እያሳየ ይገኛል። በተለይም የኮሪደር ልማት ሥራው ከተማውን በማዘመን ለኑሮ ምቹ፣ጽዱ እና ውብ እንዲሆኑ በማድረግ የከተማችንን ገጽታ የሚቀይር መሰረት በመሆን በተለይም ከተሞችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና አገልግሎቶችን ለማሳደግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛል። በገጠር እና በከተማ ያለውን የዘመናዊ አኗኗር ልዩነት በማጥበብ እንዲሁም ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንዲቻል ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉም። ከለውጡ በፊት ለከተሞች እድገት ትኩረት ባለመሰጠቱ፣ከተሞች በሚገባቸው መጠን እንዳያድጉ ምክንያት ሆነው የቆየው ቢሆንም ከተሞች የተለያዩ ማንነቶች፣እሳቤዎች፣ ዕውቀት፣ካፒታል እና ሀብት የሚንሸራሸሩባቸው መሆን ስላሉባቸው የመደመር መንግሥት ከተሞች ለሁሉም ዜጋ ምቹ መኖሪያ መሆን አለባቸው የሚል እሳቤን ይዞ የመጣውን እሳቤ በጋራ እውን በማድረግ ላይ የምንገኝና ስልጡን ከተማ (ስማርት ሲቲን) ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ከተሞች ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በትኩረትም እየተሰራ ስሆን ዲላ ከተማ አረንጓዴያማ ቦታዎችን በማልማት እና ምቹ መናፈሻዎችን እንዲሁም ከተማን የሚመጥኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እየተሰራ ይገኛል፡፡ ውብ ከተሞች የሰው ልጆች የሥራ ውጤቶች በመሆናቸው መልካም ነገር ከሠራን ጥሩ፤ ለነዋሪው ምቹ እና የዘመኑ ከተሞችን ለማየትና ለማሳየት የበለጠ ጥረቶች ይቀጥላሉ። አመሰግናለሁ!
የመሪዎች መልዕክቶች
አቶ መንግስቱ ተክሌ
የዲላ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ
ጽኑ አንድነት ለተከታታይ ድልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና የተከበራችሁ የከተማችን፣የሀገራችን ህዝቦች፣የአካባቢያችን ነዋሪዎችና የልማት አጋሮቻችን፤ ኢትዮጵያ በጀመረችው የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ትልቁ አቅማችን አንድነታችን ነው። ፓርቲያችን ብልጽግና ይፋ ያደረገው የ"ስንዴ ነዶ" ማንፌስቶ፣የተበታተነ ጉልበታችንን አስተሳስረን፣የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን አልምተንና ምርታማነታችንን አሳድገን ራሳችንን በራሳችን ለመቻል የገባነው ታላቅ ቃል ኪዳን ነው። መንግሥታችን በየደረጃው የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች በጽናት እየተጋፈጠ የህዝቡን ደህንነትና ልማት የማረጋገጥ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። ይህ ድህረ-ገጽ የለውጥ ጉዟችንን የምናጋራበት ግልጽነትን የምናሰፍንበትና የህዝባችንን ድምጽ የምንሰማበት መድረክ ነው። የ"ስንዴ ነዶው" ጥንካሬ በእያንዳንዳችን ትጋት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለሀገር ግንባታው በንቃት እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ አጋጣሚ በመቀየር፣ ኢትዮጵያን የብልጽግና ማማ ላይ እናወጣታለን! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ዋና ዋና የልማት ስራዎች
በከተማችን የሚከናወኑ ዋና ዋና የልማት ስራዎች
የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የከተማውን ወቅታዊ ማስታወቂያዎች፣ ፕሮጀክቶች እና የህዝብ መረጃዎች በቀጥታ ይከታተሉ።
የኢንቨስትመንት እድሎች
ከተማዋ ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት ዘርፎች
በዘርፉ ያሉ እድሎች
አገልገሎቶች
እንዱስትሪዎች
ግብርና
ማኑፋክቸሪንግ
ዋና የማስተዋጽኦ አጋጣሚዎች
- ፈጣን አገልግሎት
መምሪያዎች
የዲላ ከተማ አስተዳደር የሴክተር መ/ቤቶችና ሥራና ኃላፊነት
ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት
የመሬት አስተዳደር መምሪያ
የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ
የቱሪዝም መምሪያ
የሥራና ክህሎት መምሪያ
የፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
የገቢዎች መምሪያ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ
ኮርደር ልማት
እንደ ሐገር በከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ጭምር እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ቀድሞ የነበሩ ከተሞችን ገፅታ በመቀየር አዲስ ገፅታን በማላበስ ከተሞችን ውብ ማራኪና ተመራጭ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡
የኮሪደር ልማት አዲስ ኢንሼቲቭ እንደመሆኑ በአተገባበር ወቅት ዉስን ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም አሁን ላይ በመንግስት ብቻ ሳይሆን በሕብረተሰቡ ተሳትፎም ጭምር ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል
ይህ አዲስ ከተማ ፈጣሪ ኢንሼቲቭዲላ ከተማን ለነዋሪዎች ለኑሮ ምቹ እንዲሁም ተወዳደሪ ከተማ ለማድረግ እየተተገበሩ ካሉ ሥራዎች መካከል አንዱ በተመረጡ የከተማዋ አካባቢዎች የመንገድ ኮሪደር ልማት መከወን ነው።
ባለፉት ዓመታት በከተማችን የመንገድ ኮሪደር ልማት የሚከወንባቸው በቁጥር 8 ዋና ዋና ኮሪደሮችን 18 ኪ.ሜትር በላይ በመለየት የፕላን ማስጠበቅ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡
ለኮሪደር ልማት ሥራ የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ የከተማ ፕላን የማስጠበቅ ሥራ ሲሆን በዚህመ ረገድ በከተማው ነዋሪ ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም በየደረጃው ባሉ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ሥራ ከ19.2 ኪሎሜትር በላይ ፕላን የማስጠበቅ ተግባር ተከናውኗል፡፡
የከተማው ነዎሪዎች በፕላን ማስጠበቅ ተግባሩ ባደረጉት ንቁ ተሳትፎ ከመንግሥት ሊወጣ የነበረውን 654 ሚሊዮን ብር ማዳን የተቻለ ሲሆን 517 ቤቶችን በማፍረስ የከተማ ፕላን ማሰጠበቅ ተግባር በማከናወን ለቀጣይ የመንገድ ኮሪደር ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡
ከአዲስ አበባ ሞጆ ኢትዮ ኬኒያ የሚዘልቀው አስፋልት መንገድ አቋርጧት የሚያልፈው የዲላ ከተማመግቢያበር ላይ እጅግ ሳቢና ማራኪ የመግቢያ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራ በከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በኮሪደር ልማት በመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት 16 ሺህ 700ካሬሜትርተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በተመሳሳይ 8.4 Km እግረኛመንገድ ተጠናቋል፡፡
በቁጥር 5 እስናክሀውስግንባታ ተጠናቅቆ በእዚሁአከባቢ 20 ማረፊያ መቀመጫዎች ተዘጋጅተ ሕብረተሰቡ አረፍ ብሎ ነፋሻ አየር እንዲቀበልና ራሱን እንዲያዝናና አስተዋኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡
በከተማው የሚገኙ 2 አደባባዮችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የማልማት እና የማስዋብ ሥራ ተሰርቶ 4ኪ.ሜ የመንገድ መብራት ማስዋብ ሥራ ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡.
የኮሪደር ልማት ከተማን እንደ አዲስ ከነፍጠር ባሻገር ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል በመፍጠርም አበርክቶቱ ከፍተኛ ሆኖ በዲላ ለ1ሺህ 205 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
የዲላ ከተማ የኮሪደር ልማትን በማስቀጠል በከተማዋ ክልል ዋና ዋና መንገዶች ላይና አደባባዮች ብሎም ሰው ሰራሽ ሐይቅም ጭምር በመስራት አዲስ ከተማ የመፍጠሩ ተግባር ከነዋሪዎቻችን ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ዲላ በለውጥ ምዕራፍ ላይ ናት!
እንኳን ወደ ዲላ ከተማ አስተዳደር ይፋዊ የድረ-ገጽ መረጃ ቋት በሰላም መጣችሁ!
የከተማችን
አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ዋነኛ ዓላማ በመንግስትና በህዝብ መካከል የታመነ ድልድይ በመሆን፣ የዲላን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ለነዋሪዎቻችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ ነው።
ዲላ
በለውጥ ምዕራፍ
ላይ ናት!
በአሁኑ
ወቅት በከተማችን በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የሚከናወኑ፦
- የኮሪደር ልማት
ስራዎች፣
- የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች ግንባታ
እና
- ሌሎች ግዙፍ
የመሠረተ ልማት
ስኬቶች የከተማችንን
ገጽታ ከመቀየር
ባለፈ ለነዋሪዎቻችን
ምቹ የኑሮ ሁኔታን
እየፈጠሩ ይገኛሉ።
የዲጂታል
ሚናችንና ግባችን፦
- ወቅታዊ መረጃ፦ የልማት
ስራዎችንና የመንግስት
ውሳኔዎችን በታማኝነት
ማጋራት።
- የመረጃ ሉዓላዊነት፦ በከተማችን
ሰላምና ልማት
ላይ የሚነዙ የተዛቡ
መረጃዎችን (Misinformation) በእውነተኛ
መረጃ መመከት።
- ሁለትዮሽ ግንኙነት፦ የመንግስትን
ድምፅ ማስተማር
ብቻ ሳይሆን፣ የህዝቡን
ቅሬታና ጥቆማ
የምንቀበልበት ክፍት
መድረክ መሆን።
የክብር
ጥሪ፦
የዲላ
ከተማ ነዋሪዎችና የከተማችን ወዳጆች በሙሉ፤ ይህንን ድረ-ገጽ እንደ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ በመጠቀም ለከተማችን ዕድገትና ሰላም ገንቢ አስተያየታችሁን እንድታካፍሉን ጥሪዬን አቀርባለሁ።
መረጃ
የልማት መነሻ
ነው!
የፎቶግራፍ አምዶች
የከተማችንን ውበት ያስሱ
ምንም ፎቶ አልተገኘም
/